Sunday, December 6, 2015

የሃገራችን ወጣቶች ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራስያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ጋር በመሰለፍ ላይ መሆናቸው ወኪላችን ከማሰልጠኛ ማእከል ገለፀ።



      የአምባገነኑን የኢህአዴግ ስርዓት በመቃወም ከተለያዩ የሃገራችን  ክፍሎች ተነስተው ከትህዴን ጋር የሚሰለፉ ወጣቶች ቁጥራቸው እየበዛ መሄዱን ወኪላችን ከትህዴን ማሰልጠኛ የገለፀ ሲሆን  በዚህ ሳምንት ብቻ ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ የተቀላቀሉ  ወጣቶች የተወሰነ ስም ዝርዝራቸው ለመጥቀስ ያህል፦     
   ባህበሎም ገብማርያም።ከማእከላዊ ዞን አሕፈሮም  ወረዳ ማይ ሓማቶ ቀበሌ፤
   ብርሃን ገብረመድህን ከማእከላዊ ዞን አሕፈሮም  ወረዳ ሆያ ቀበሌ፤
   ሰለሞን ገዌ ከኦሮምያ ክልል ምስራቕ ሽዋ ዞን መቂት ወረዳ፤
   አፍሬም ጉዕሽና ሚኪኤለ  ገብረሚኪኤል ሁለቱም ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ዓዲ ፍታው ቀበሌ  የሚባሉ የሚገኙባቸው ናቸው፣
      በተለይ  አፍሬም ጉዕሽና ሚኪኤለ  ገብረሚኪኤል  ከትህዴን ጎን ተሰልፈው ሊታገሉ የፈለጉበት ምክንያት ሲገልፁ እኛ  አቅመ ኣዳም ደርሰን እያለን መሬት ልናገኝ ኣልቻልንም ወደ ስደት ለመሄድ ኣስበን ነበር በመጨረሻ ግን ወደ ስደት መሄድ መፍትሄ እንዳልሆነ ስለ ተረዳን  ክትህዴን ጎን ታጥቀን  በመሰለፍ ግፈኛወን የወያነ ኢህአዴግ ስርአት  መዋጋት ኣለብን ብለን ወስነናል ሲሉ ገልፀዋል፣
   ሰለሞን ገዌ በበኩሉ በንግድ ስራ ተሰማርቶ የግል ኑረውን ለማሸነፍ በሚሰራበት ግዜ የስርኣቱ ተላላኪዎች  ግን የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላት  በቤትህ ውሽጥ ይሰበሰባሉ የሚል የሃሰት ዉንጀላ በማቅረብ ወደ ዙዋይ በመውሰድ ለሁለት ኣመት ያክል ማስረጃ በሌለው  ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ መታሰሩን  ከገለፀ ብሃዋላ  ከእስር ቤቱ ጉቦ ከፍሎ ለማምለጥ  እንዳቻለ ጠቁሞ በዚህ እስር ቤት የሚገኙ ዎጎኖቻችን ህግ ኣስከባሪዎች ነን  በሚሉ የስርኣቱ ካድሬዎች  በዱላ  እየተደብደብቡ  ኣስከፊ   ስቃይ   እያሳለፉ መሆናቸውን ገለጠ።