Saturday, December 19, 2015

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዓዲ አርቃይ ወረዳ ልዩ ቦታ ጨው በር በሚባል አካባቢ በዚህ ሳምንት በስረአቱ ፓሊስና ጠመንጃ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች መካከል በተደረገ ውጊያ በርከት ያሉ የፓሊስ ሃይል እንደሞቱ ምንጮቻችን ገለፁ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዓዲ አርቃይ  ወረዳ ልዩ ቦታ ጨውበር በሚባል አካባቢ በኢህአዴግ ሰረአት ፓሊሶችና የገዢውን ሰረአትን በመቃውም በረሃ ወጥተው በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች መካከል በዚህ ሳምንት ውስጥ በተደረገ ወጊያ ኮንስታብል አሸናፊ የተባለ የሚገኝባቸው ፖሊሶች በውጊያው እንደሞቱና ሌሎቹም  ከባድና ቀላል የመቆሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት ለማውቅ ተችሏል።
  ይህ በእንዲህ እንዳለ በጊዜው  ስርአቱን የተቃወሙት ሰዎች  ከስረአቱ  ታጣቂዎች ጋር ገጥመው ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለፀው መረጃው የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት አብዛኛው ኗዋሪው ህዝብ ከጎናቸው በመሰለፋቸውና  በመተባበራቸው ምክንያት በላያቸው ላይ ሊመጣ የሚችል ጉዳት ሊቀንስ እንደቻለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷዋል።