Saturday, December 19, 2015

ገዥው የኢህአዴግ ስርአት በኦሮምያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ዓመፅ ለመበተን በማለት ያሰማራቸው ወተሃደሮች ወደ ወገናችን ጥይት አንተኩስም በማለት ትጥቃቸው በመጣል ወደ ህዝብ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ታወቀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ ገዥው የኢህአዴግ ስርአት ኣዲሱ የአዲስ ኣበባና የአከባቢዋን ማስተር ፕላን ብሎ ህዝብ ያላመነበት ባወጣው ኣዋጅ ምክንያት የተነሳ፣ በክልል ኦሮምያ በሚገኙ 150 ከተማዎች አዋጁን የመቃወም ሂደቱ እየተቀጣጠለ መሆኑን የሚታወቅ ሁኖ በታህሳስ 2/ 2008 ዓ/ም ብቻ  በምእራብ ሽዋና በደቡብ ምእራብ ሽዋ በተነሳው ህዝባዊ ዓመፅ 25 ንፁሃን ወገኖቻችን እንደተገደሉ ተገለፀ።
    በመላው የኦሮምያ ክልል ኣከባቢዎች የተነሳ ህዝባዊ ኣመፅ፣ ህዝቡ የወጣው አዲሱ አዋጅ በጠነከረ ሁኔታ በመቃወሙ የሰጋው የኢህአዴግ ስርአት፣ ህዝባዊ አመፁን ለማብረድ ብሎ ያሰማራቸው ወታደሮች በበኩላቸው ወደ ወገኖቻችን ጥይት ኣንተኩስም፤ በህወሓት ካድሬዎች ብቻ የሚመራው የመከላከያ ሚኒስተር ትእዛዝ አንቀበልም እያሉ የለበሱትን ወታደራዊ ደምብ ልብስ  በማውጣት በየጎደናው በእሳት እንዳቃጠሉትና ትጥቃቸውን እየጣሉ ወደ ህዝቡ እየተቀላቀሉ  መሆናቸውን ለማወቅ ተችለዋል።
    ይህ በኦሮምያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በታህሳስ 3/ 2008 ዓ/ም በምእራብ ሽዋ ባኮና በምእራብ ወለጋ ነጆ፣ በወራ ጅራ ወረዳ፤ በኣንቹማ ጎሪንና በጊዳን ከተማ ተቃውሞው በመቀጣጠል ላይ መሆኑን የገለፀው መረጃው፣ በቡራዩ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ወታደሮችን ወደ ቅጥር ጊቢው እንዳይገቡ መንገዱን በድንጋይ  እንዳጠሩት ታዉቀዋል።
   አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአት ለተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት በሃይል ለመበተን ትእዛዝ  ቢያወርዱም አመፁ እየተባባሰ እንጂ ሊበርድ እንዳልቻለ የደረሰን መረጃ ኣስረድተዋል።