Tuesday, June 21, 2016

በአነስተኛና መካከለኛ ተቋሞች የሚሰማሩ ወገኖችን ለማገዝ ተብሎ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኃላፊነት የወሰደው 4.8 ቢሊዮን ብር ጥቅም ላይ ሳይውል እንደባከነ ታወቀ።



   በተገኘው መረጃ መሰረት፣በአነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ለተሰማሩ ዜጎች በማምረት ላይ ለሚያጋጥማቸው የማሽነሪ ችግሮች ለመፍታት ፣የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገንዘብ ለማቅረብ ኃላፊነት በመውሰድ በ2008ዓ.ም ለዚህ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ ተብሎ 4.8 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድሩ ብቁ የሆነ ኢንተርፕራይዝ አዘጋጅቶ ሊያቀርብ እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል።
   በመጨረሻም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በኢትዮጵያ  ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዳሏትና የእነዚህንም ብዛት ወደ 3 ሚሊዮን ለማሳደግ እቅድ የተያዘ ቢሆንም ይሁን እንጂ ኢንተርፕራይዞቹ ለማሽን መግዣ የሚሆን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበዳሪዎቹን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ማሽኖች እንዲቀርብላቸው  እቅድ ተይዞ እንደነበር ከገለፀ በኋላ ይሁን እንጂ የተያዘው በጀት በተለያዩ ምክንያቶች ባክኖ መትረፉንና ሊተገበር ባለመቻሉ ሥራ አጥነት በሰፋ መልኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment