Thursday, June 9, 2016

በሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ወረዳ የሚገኙ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ከርእሰ መምህራን ጋር ሽርክና በመፍጠር በሙስና ዉስጥ መዘፈቃቸው ከአከባቢው የደረሰን መረጃ ኣመለከተ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሳዕሲዕ ፃዕዳ  እምባ ወረዳ የሚገኙ የትምህርት ቤት ሃላፊዎች ለስራ ማስከጃ እየተባለ በየአመቱ የሚመደበው ገንዘብ  ከርእሰ መምህራን ጋር በመመሻጠር  የህዝብ ገንዘብ በማባከን ስራ ላይ መሰማራታቸው  የገለፀው መረጃው። በመሆኑም  ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች  ለስራ ማስከጃ ታስቦ ከተማሪዎችና ከሌሎች ገቢዎች የተገኘው 6 ሚልዮን ብር ከአከባቢው አስተዳዳሪዎች ሽርክና በመፍጠር  ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት  ታውቀዋል።
     መረጃው ጨምሮ ህብረተቡ የህዝብ ገንዘብ የሚያባካኑ ባለስልጣኖች በህግ እንዲጠየቁ ያቀረበው ኣቤቱታ ሰሚ ጀሮ  ማጣቱና በዚህ ሳብያም በስርአቱ መጥፎ ተግባር ላይ በማማረር  እንደሚገኝ ተገለፀ።

No comments:

Post a Comment