Thursday, February 2, 2017

በጥልቀት እንታደስ በሚል ምክንያት በምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ስብሰባ ምንም ውጤት ሳይሰጥ በጥር 27 ቀን 2009 ዓ/ም እንደተጠናቀቀ በስብሰባው የተሳተፉ ምንጮቻችን ገለፁ።



   ጥር 27 ቀን በነበረው መድረክ በስብሰባው ተሳፊዎች ስብሰባውን በሚመሩት ካድሬዎች ላይ ከባድ ጥያቄዎች እንደተነሱ የገለፁት ምንጮቻችን፤ በተለይም  የውሃ ሃብት ቢሮ፤ የኮንስታክሽን ቢሮ፤ የመሬት ዲስክ ቢሮ፤ የፍትህና ፀጥታ ቢሮ በጀት በማጠፋፋት፤ ወንጀልን በመደበቅና ፍትህን በማጓደል ከፍተኛ ሙስና የፈፀሙ ተብለው የተገመገሙ ሲሆን፤ በኣጠቃላይ ደግሞ የወረዳው በጀት የት እንደሚገባ ኣይታወቅም የሚሉ ሰፋፊ እና ኣከራካሪ የሆኑ ጥያቄዎች ከህዝብ እንደቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።
    የ2009 ዓ/ም በጀት የፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ ለመስራት ወጭ  ከተደረገ 4 ሚሊዮን ብር ውጭ ሌላው በጀት በህዝብ ጥቅም ላይ እንዳልዋለና፣ ከደውሃን ወደ ወርኣትለና እንዳልጌዳ የተዘረጋ መንገድ በጣም ችግር እንዳለውና ትክክለኛ ኣፈር እንዳልተመረጠለት እንዲሁም ጥናት ስላልተደረገለት  በህዝብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ እንደፈጠረ ታውቋል። ይህ እንዳለ ሁኖ በእንዳልጌዳ ማሀል የተሰሩትን 121 የሚሆኑ ህጋዊ ያልሆኑ ቤቶች ለብዙ ኣመታት መፍትሄ አጥቶ ህዝቡ በከባድ ጭንቅና ችግር እንዳለ የገለፁት ምንጮቻችን፤ በፍትህ በኩልም የሃብታሞችና ሃላፊዎች መዝገብ እንደማይታይ፤ ለምሳሌ ደግሞ የዓለቲና ቀበሌ ኣስተዳደር ባራኺ ተስፋይ ከኢሮብ ወረዳ ኣስተዳደር ጋር ተመሻጥሮ የወሰዱት የህዝብ እህልና ገንዘብ ሳይጣራ መዝገባቸው እንደተዘጋና በመድረክ ላይ የተገመገመ እንኳን ቢሆን በቂ መልስ ሳያገኝ እንደታለፈ ታውቋል።
    በመጨረሻም  የኢሮብ ወረዳ ህዝብ  ግማሹ ከወረዳው ኣስተዳደር ጋር ግማሹ ደግሞ ከወረዳው አፈጉባኤ ጋር በመሆን በሁለት ቡድን ተከፍሎ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል። 




No comments:

Post a Comment