Friday, July 21, 2017

በናዕዴር ዓድየት ወረዳ ሰመማ ከተማ የሚገኙ መምህራን መንግስት መኖርያ ቤት ለመምህራን ትሰጣላችሁ ቢልም፣ እስካሁን ግን ሊሰጠን አልቻለም ሲሉ ገለፁ።



በመረጃዉ መሰረት የኢህአዴግ ስርአት በአሁኑ ወቅት የመምህራን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት እየሰራሁ ነዉ ቢልም፣ እስካሁን ግን እንዲያድላቸዉ በተደጋጋሚ ጠይቀዉ፣ ሰሚ እንዳጡ በናዕዴር አዴት ወረዳ ሰመማ ከተማ የሚገኙ በማህበር የተደራጁ መምህራን ምሬታቸዉን በመግለፅ ይገኛሉ።
በአከባቢዉ የተወሰኑ መምህራን መኖርያ ቤት ተሰጥተዉ ሲያበቁ፣ በኛ ሲደርስ ግን  መከልከሉ አሳዛኝ ፍፃሜ ነዉ ያሉት አሰተማሪዎቹ፣ይህ ደግሞ ስርአቱ እየፈፀመዉ ያለ አድሎ መሆኑና፣ የስርአቱ አባል የሆነ ሰዉ ጥቅማ ጥቅም እንዲያገኝ አባል ያልሆነ ደግሞ ማግኘት እንደማይችል፣ በግልፅ የሚያሳይ ነዉ በማለት፣ መምህራኖቹ አክለዉ ገልጽዋል።

No comments:

Post a Comment