Saturday, July 1, 2017

በቋራ ኣካባቢ ሶስት ኦራል የኢህአዴግ ወታደራዊ ተሽካርካሪዎች ወታደሮች ጭነው በሚጓዙበት ጊዜ በአካባቢው መሳርያ ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን እየተገለፀ ነው።



  መረጃው እንዳመለከተው ቅዳሜ ሰኔ 17 2009 ዓ.ም የወያኔ ኢህአዴግ ሰራዊት ጭነው እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሶስት ኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በአከባቢው እየተንቀሳቀሱ በነበሩ ወጣቶች በወሰዱት ድንገታዊ እርምጃ ሙሉ በሙሉ እንደጋዩት የታወቀ ሆኖ፣ በርከት ያለ ወታራዊ ቁሳቁሶች ማለት እንደ መትረየስ፣ስናይፐር፣ የእጅ ቦቦችና በርከት ያሉ ጥይቶች እንደተማረኩ ገልጿል።
 በመጨረሻ የኢህአዴግ ሰራዊት በቆራ ኣከባቢ በደረሰው ድንገታዊ የማጥቃት እርምጃ በደረሰው ቅጭት ሌላ ሰራዊት ወደ ቦታው በመላክ ጥቃት ለማዉረድ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ ኣመልክቷል።


No comments:

Post a Comment