Monday, August 7, 2017

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ለታካሚዎች የሚገባ አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ ተገለፀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት በመቐለ ከተማ የሚገኝ ሪፈራል ሆስፒታል ዓይደር ባጋጠመው የባለሞያዎችና የማተርያል እጥረት ምክንያት፣ ለሁሙማን ተገቢ አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ጊዜ በሆስፒታሉ ከተለያዩ የትግራይ ቦታዎች የመጡ በርካታ ሁሙማን መኖራቸው የገለፀው መረጃው፣ ይሁን እንጂ በሆስፒታሉ  የባለሞያዎችና እልጋ እጥረት በመኖሩ፣ በሽተኞች ተገቢ አገልግሎት ለማግኝት እንዳልቻሉ  በርካታ ወገኖች በመግለፅ ይገኛሉ።
በተጨማሪ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከልክ በላይ ታካሚዎች ከመያዙ ባሻገር በጣም ለጠናቸዉ በሽተኞች ቀልጣፋ እርዳታ ሊሰጥ እንዳልቻለና በሆስፒታሉ በለው የአልጋ እጥረት ምክንያት፣ በሽተኞቹ በመሬት እየተኙ ላልተፈለገ ተጨማሪ በሽታና ስቃይ እየተጋለጡ እንደሚገኙ፣ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
 

No comments:

Post a Comment