Monday, April 22, 2013

በአማራ ክልል በአዊ ዞን ፤ ጃዊ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በተካሄደው የማማያ ምርጫ መላው ኗሪው ህዝብ በፍላጎቱ ያልተሳተፈበት ቢሆንም የተወሰኑት ኗሪዎች በፖሊስ ሃይል ከመኖሪያ ቤታቸው ተገደው በመውጣት እዲመርጡ መደረጉን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በቃቲ ዘረገነት የቀበሌ 01 ኗሪ ህዝብ በሃይል ተገዶ እንዲወጣ ካደረጉ ካድሪዎች መካከል
1-አቶ አወቀ ሞላ
2-አቶ ሞት ባይኖር ትንሻው
3-አቶ አዳነ ክንፈ
የሚገኙባቸው ሲሆን እነዚህ ካድሬዎች ከሌሎች በርካታ ካድሬዎችና የፖሊስ አባላት ጋር በመተባበር ህዝቡን ሳይወድ በግድ ከመኖሪያ ቤቱ እንዲወጣ በማድረግ በምርጫው ድምጹን እንዲሰጥ አድርገዋል፣
የአከባቢው ኗሪ ህዝብ ድምጹን መስጠት ያልፈለገበት ዋና ምክንያት ኢህአዴግ በብቸኝነት በሚወዳደርበትና ሌሎች አማራጭ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ እድሉ ስላልተሰጠን ነው በማለት ይገልጻሉ፣
ከምርጫው ጋር በተያያዘ የአከባቢውን ህዝብ በምርጫው እንዳይሳተፍ አነሳስታችሃል በሚል ሰበብ በኢህአዴግ ስርዓት ከታሰሩ የአከባቢው ኗሪዎች መካከል ።-

1-ዮሴፍ ግጃ
2-መምህር ሚልክያስ ፓስታ
3-አዳነ ካሳ
4-ጨንቃኖ አያና
5-ኤልያስ አርባስ
6-በቀለ ካሳ
7-ማትዮስ ዱማ
8-በርሲሳ ባርሳ
9-ታደሰ ሻራ አትንኩት
ሲሁኑ እነዚህ ሰዎች ህዝቡ ህጋዊ መብቱን ተጠቅሞ አንመርጥም በማለቱ እንደ ወምጀለኛ ተቆጥረው ምንም የፈጸሙት ወንጀል ሳይኖር ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑ ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላል፣
በተመሳሳይ በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ በወንበርማ ፤ ቡሬና ፍኖተ ሰላም ወረዳዎች የተካሄዱ የሟሟያ ምርጫ መላው የአካባቢው ህብረተሰብ አንመርጥም በማለት ከምርጫው እራሱን ማግለሉን ቷውቃል፣
    ህብረተሰቡ እንዲህ ባለው የይስሙላ ምርጫ በመሳተፍ አምባገነኖችን ማበረታታት አይገባንም በማለት እራሱን ከምርጫ ማግለሉን ተገቢ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ፣