Tuesday, November 19, 2013

በህወሓት የስራ አስፈጻሚ አካል መካከል የተፈጠረው የስልጣን ስግብግብነትና መናናቅን መሰረት ያደረገ ውጥረት እየተባባሰ መጣ፣




ልዩነቱ በዋናነት የሚታየው በክልሉ ፕረዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ በአንድ በኩል በምክትል ፕረዚደንትነት እያገለገሉ ያሉት አቶ ኪሮስ ቢተውና አቶ በየነ መኩሩ ደግሞ በሌላ በኩል ሆኖ አቶ አባይ ወልዱ በስሩ የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት ይንቁኛል ከሚል ስሜት ተነስቶ ከስልጣናችሁ ትነሳላችሁ በማለት በሃይል አስፈራርቶ ለመምራት ሲሞክር አቶ ኪሮስ ቢተውና አቶ በየነ መኩሩ ደግሞ አንተ ክልሉንም ሆነ ህወሓትን ለመምራት ብቃቱ የለህም ከስልጣን የመነሳት ጥያቄ ከመጣ በቀዳሚነት አንተ ካለህበት ስልጣን መነሳት አለብህ ሲሉ እንደመለስሏቸውና በዚህም በመካከላቸው አለመግባባት እያየለ መምጣቱን ቷውቋል፣
በአመራሩ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት ቀደም ሲል የአምስት ዞን መስተዳድር በተገኙበት የተደረገውን ሙከራ ውጤት ባለማስገኘቱ በያዝነው ሳምንት በተደረገው ተመሳሳይ ስብሰባም ሊግባቡ ባለመቻላቸው ቅር የተሰኙ የዞን አስተዳዳሪዎች ከመለስ ሞት ብሁዋላ በስልጣን ስግብግብነት መነታረክ ጀመራችሁ ሲሉ መደመጣቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣