Tuesday, November 19, 2013

በመንግስት ተገደው በብድር የወሰዱትን ማዳበሪያ ዋጋና ወለድ ተሎ እንዲመልሱ የተገደዱ የሑመራና አከባቢዋ ኗሪዎች ኑራችንን መምራት አልቻልንም ይላሉ፣




የሑመራና አከባቢዋ ኗሪዎች ካለፍላጎታቸው በመንግስት ተገደው የወሰዱት ማዳበሪያ ተጠቅመው የእርሻ ስራቸውን ቢያከናውኑም በወቅቱ በነበረው የዝናብ እጥረት ምክንያት እዳቸውን ለመክፈል የሚያስችላቸውን ምርት ማግኘት አልቻሉም፣ መንግስት የገበሬውን ችግር ተገንዝቦ የእፎይታ ጊዜ መስጠት ሲገባው የወሰዱትን ማዳበሪያ ዋጋ ከነ ወለዱ አሁኑኑ እንዲመልሱ ስላስገደዳቸው ኗሪው በችግር ላይ ይገኛል፣
ኗሪው ተሎ እዳውን ካመጣ አምጥቶ እንዲከፍል በስርዓቱ ካድሬዎች እየተደረገበት ያለ ጫናና የማስገደድ እርምጃ በቤተሰብ ውስጥ ዘልቆ በመግባት በባልና ሚስት መካከል ከፍተኛ ንትርክ እየተፈጠረ ሲሆን በዚህም አቶ ሰለሞን የተባለ የአከባቢው ኗሪ ስሜቱን መቆጠጣር ተስኖት ድንገት በሰነዘረው ዱላ ህዳር 6,2006 ዓ/ም በሚያሳዝን ሁኔታ የልጆቹን እናት መግደሉን ቷውቋል፣