በመረጃው መሰረት በሸራሮ
ከተማና አካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች ያላቸውን የኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት፤ በኮብልስቶን መንገድ ስራ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ ተብሎ፤
ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ ተማሪዎች ቢመለመሉም፤ አስተዳዳሪዎቹ ግን ስራውን ለመስራት ተወዳድረው ያለፉትን አስቀርተው፤ ቤተሰቦቻቸው
ለሆኑትና ጉቦ ለሚሰጧቸው ሰዎች ብቻ ወደ ስራው እያስገቧቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮ እነዚህ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተወዳድረው ያለፉትን ተማሪዎች
የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ሰብስበው ስራ የለም ወደየ ቀበሌያችሁ ሂዱ ብለው ስለተናገሯቸው፤ ወጣት ተማሪዎቹና ህብረተሰቡ በአስተዳዳሪዎቹ
ላይ ምሬታቸውን እያሰሙ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል፣