Saturday, May 9, 2015

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን በሚገኙት አብዛኛዎቹ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ የትህዴን ፓምፕሌት በመበተኑ ምክንያት የህወሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች በከባድ ጭንቀት መውደቃቸውን ምንጮች ከአካባቢው ገለፁ።



    በትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ የተዘጋጀው ወቅታዊ መልእክት የያዙ ፓንፕሌቶች ሚያዝያ 29 /2007 ዓ/ም ንጋት ላይ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ውስጥ- በአውተቡስ መናሃርያ፤ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ሌሎች መንደሮች በተበተኑበት ሰዓት ፓምፕሌቱ ወደ ህዝቡ መድረሱን የረጋገጡት የስርዓቱ ካድሬዎች ሚያዝያ 29/ 2007 ዓ/ም መደበኛ ፖሊስና የፌደራል ፖሊስ በማሰማራት መኖርያ ቤቶችንና ሲንቀሳቀስ ያገኙትን ሰው ህጋዊ ያልሆነ ወረቀት ይዛቿል እያሉ በመፈተሽ ላይ መዋላቸውን መረጃው አስታውቋል።
    በተመሳሳይ ሚያዝያ 29/ 2007 ዓ/ም በአዲ ዳዕሮ ከተማ ውስጥ እውቶብስ መናሃርያና ፒያሳ ላይ ብዛት ያላቸው ፓምፕሌቶች ተበትነው በከተማው ህዝብና በተለያየ ስራ ምክንያት ወደ ከተማው በመጡት የገጠር ነዋሪዎች እጅ መግባቱን የታዘቡት የከተማው አስተዳዳዎች ነዋሪውን ህዝብ ሚያዝያ 30/2007 ዓ/ም ላይ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት የትህዴን ፓምፕሌት ይዞ የተገኘ ሰው ከባድ እርምጃ ይወሰድበታል ብለው እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በንዲህ እንዳለ በዚሁ ተመሳሳይ ቀን በሸራሮ ከተማ አውቶብስ መናሃርያ፤ እንዳመድሃኒአለም፤ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤትና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች የትህዴ ፓምፕሌቶች ተበትነው በነዋሪው ህዝብ፤ ተማሪዎችና መጤ እንግዶች መድረሱን የገለፀው መረጃው ህዝቡ በድርጅቱ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተስፋ ማሳደሩን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።