Sunday, April 27, 2014

በአፋር ክልል በዒሳን ብሄረሰብና ከኢትዮጵያ ሶማሌ በሃውያን ጎሳዎች መካከል ሚያዚያ 11/2006 ዓ.ም በተፈጠርው ግጭት በርከት ያሉ ወገኖች ለሞትና ለአካል ጉዳት ሰለባ እንደሆኑ ታወቀ።



በሚያዚያ 11/2006 ዓ.ም በአፋር ክልል ገዋኒ ወረዳ መተኻ ቀበሌ የሚገኙ የኒሳን ብሄረሰብና በሶማሌ ክልል በሚገኙ ሃውያን ጎሳ መካከል በተፈጠርው ግጭት ከአፋር ክልል ብሄረሰብ 8 ሰዎች እንደሞቱና 9 ሰዎች ደግሞ በከባድ የቆሰሉ ሲሆን ከሶማሌ ክልል ሃውያን ጎሳ ደግሞ 9 ሰዎች ሲሞቱ 5 በካባድ እንደቆሰሉ ካአካባቢው በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏዋ።
   መረጃው ጨምሮ እንደአስረዳው ለዚሁ ጉዳይ እንዲያረጋጉ ተብለው ወደ ቦታው የተንቀሳቀሱ የወያኔ ኢህአዴግ የፌደራል ፖሊስ አባላት የነበረውን ግጭት ከማረጋጋት ይልቅ ከሶማሌ ‘ክልል ሃውያን ጎሳ ጋር በመወገን የአፋር ክልል ተወላጆችን እንደተዋጓቸውና በነበርው የተኩስ ልውውጥም ከፌደራል ፖሊስ አባላት 3 ያክል መሞታቸውን መረጃው አስታውቋል።
  ይህ በእንዲህ እንዳለ የስርዓቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የፌደራል ፖሊስ አባላት የሃውያን ጎሳዎችን በመደገፍ በአፋር ተውላጆች ላይ የፈፀሙትን በደል ከህዝብ አይን ለመደበቅ ሲሉ በአስቸኳይ በአካባቢው የነበሩትን የፌደራል ፖሊስ አባላት ከስፍራው እንዲነሱ እንዳደረጉና በነበረው የተኩስ ልውውጥም የተገደሉትን 3ት የፈደራል ፖሊስ አባላት በውጊያው ላይ ያልተሳተፉ ለማስመሰል ወዲያውኑ ደብዛቸውን እንዳጠፋቸው ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
   በተጨማሪ የአፋር ክልል ተወላጆች የነበረውን ግጭት ከማረጋጋት ይልቅ ከሃውያን ብሄረሰብ ጋር በመወገን ጥይት በመተኮስ በላያቸው ላይ ጉዳት ያደረሰባቸውን የፌደራል ፖሊስ በመቃዎም ወደሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በመሄድ እንዚህ ወንጀለኞች በህግ ፊት ቀርበው ተገቢ የሆነ ቅጣት እንዲሰጣቸው በማለት ላቀረቡት አቤቱታ የመንግስት ባለስልጣናት ግን የምናውቀው ነገር የለም የምትሉት ነገርም ፍፁም ሐሰትና የፌደራል ፖሊስ እጅም አልነበረበትም ብለው ኣስተባብለዋል።