Sunday, April 27, 2014

በምስራቃዊ ትግራይ ዞን አዲግራት ከተማ የሚገኙ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ያጋጠማቸውን የምግብ አቅርቦት እጥረትና የመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት በማድረግ የተቃውሞ አድማ ማድረጋቸው ተገለፀ።



የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቋሙ ተብሎ የሚወጣው ገንዘብ  በኃላፊዎች ስለባከነ ለማህበራዊ ችግር መጋለጣቸውን የገለፀው መረጃው በተለይ የጥዋት ቁርሳቸው በመቅረቱ በመማር ማስተማር  ሂደቱ ላይ ከባድ እንቅፋት ስለፈጠረባቸው ተቃውሞ እንዲያካሂዱ ምክንያት እንደሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።
     መረጃው በማስከትል በተማሪዎቹ የቀረበው ጥያቄም የማህበራዊ ችግር አለ፥ የትምህርት ጥራት የለም፥ ሆን ብላችሁ ተማሪ እንዲወድቅ ታደርጋላችሁ፥ የሚሉና ሌሎች ተቃውሞዎች በማሰማታቸውና በመገምገማቸው ምክንያት። ይህንን መሰረት በማድረግ የዩንቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጋይም እናስተካክላለን የሚል ምላሽ ቢሰጥም እስካሁን የታየ ለውጥ አለመኖሩን ተገለፀ።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩንቨርሲቲው ባለው የማህበራዊ ችግርና ሙስና ምክንያት ከ170 የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች መካከል 30ዎቹ ሲያልፉ 140 ተማሪዎች እንደወደቁ ለማወቅ ተችሏል።
    በተመሳሳይ ሚያዚያ 2 ቀን 2006 ዓ/ም በተማሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር የገለፀው መረጃው የግጭቱ መነሻም የስርዓቱ ተላላኪ በሆኑ መምህራን መሆኑ እየታወቀ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት በሚል አስመሳይ ስብሰባ በረዳት ፕሬዘዳንቱ ዶ/ር አይናለም መድረክ መሪነት መካሄዱንና ተማሪዎችም “ይህ ጥላቻ ሆነ ብላችሁ እራሳችሁ የፈጠራችሁት ስለሆነ እኛ የምንገመግመው ነገር የለም! ግን ደግሞ መፍትሄ እናስቀምጥለታለን” በማለት ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ መረጃው አክሎ አስረድቷል።