በ22ኛ
ክፍለጦር በስታፍ ውስጥ እየሰራ የነበረው መቶ አለቃ ደረጀ ካሳየ የተባለው መኮንን መጋቢት 28/ 2006 ዓ/ም የተገደለ ሲሆን
አባላቱ ገዳዩ ተይዞ ለምን ወደ ፍርድ አይቀርብም ብለው ቢጠይቁም ጉዳዩ ተደበስብሶ እንዲቀር የሚፈልጉ የክፈለጦሩ አዛዦች ግን ጥያቄ
ላቀረቡ አባላት አድመኞች በሚል ምክንያት ከወር ደሞዛቸው 5% ቀጥተው ከነበሩበት ክፍል አስወጥተው እንደበተንዋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
በመረጃው መሰረት እነዚህ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ አድመኞች
ተብሎው የተቀጡና ከክፍላቸው ወጥተው እንዲበታተኑ የተደረጉ የሰራዊት አባላት መቶ አለቃ አስራት ተሾመ፤ አስራ-አለቃ አቡ ማርቆስና
ሌሎችም እንደሆኑና የተወሰደው እርምጃም በመላው የክፍለጦሩ የሰራዊት አባላት መነሳሳት እንዳስከተለ መረጃው አክሎ እስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሻለቃ መብራህቱ የተባለው የ 8ኛ
ሜካናይዝድ የመረጃ ሃላፊ ሰራዊቱን በማነሳሳትና ጥይት በመሸጥ ውንጀላ ተከሶ አዲ ኮኾብ በተባለው የእዙ እስርቤት ውስጥ ታስሮ
እንደሚገኝ ከእስርቤቱ ውስጥ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።