Monday, April 28, 2014

በማእከላዊ እዝ የ31ኛ ክፍለ-ጦር ሰራዊትን እያነሳሳችሁ ነው የተባሉት መኮነኖች የሚገኙባቸው በርከት ያሉ የሰራዊቱ አባላት መጋቢት 26/ ቀን 2006 ዓ/ም እንደታሰሩ ተገለፀ።




በመረጃው መሰረት የወታደሮቹ መታሰር ምክንያት በክፍለ-ጦሩ ለሚገኙ የሰራዊቱ አባላትን የ7 አመት አገልግሎት አንፈርምም እንዲሉ አነሳስታችኋል በሚል እንደሆነና ታስረው ከሚገኙት የሰራዊቱ አባላትም ሻንበል ብሳሳ ጭሉ የተባለው በ31ክፍለጦር የአንደኛ ሬጅመንት አዛዥ፤ መቶ አለቃ አብርሃ ተስፋይ ከ2 ሬጅመንት፤ አምሳ አለቃ አስረስ ባዩ ከሁለተኛ ሬጅመንትና ተራ ወተሃደር ሽዋንግዛው ታምራት ከሬጅመንት ሰዎስት ሲሆኑ በባድመ አካባቢ ታስረው እንደሚገኙ ከቦታው ሸልኮ የደረሰን መረጃ አክሎ እስረድቷል።