Monday, April 28, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ማይ ካድራ ከተማ በመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት እለታዊ ኑሮአቸውን ሊመሩ ባለመቻላቸው በስርአቱ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ መሆናቸው ተገለፀ ።



በመረጃው መሰረት በማይ ካድራ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች በመብራትና በሌሎችም የመሰረተ ልማት እጥረቶች ምክንያት የተለያዩ የግል ባለ ሃብቶች የጀመሩትን ስራ ሊያቛሩጡት እየተገደዱ በመሆናቸው ላጋጠማቸው ችግር መፍትሄ እንዲደረግላቸው በማለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ቃል ከመግባት ያለፍ የተሰጣቸው መፍትሔ እንደሌለ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ለማይ ካድራ ነዋሪዎች ለማታለል ተብሎ  ከሦስት አመታት በፊት የተወሰኑ የኤሌክትሪክ ሞሶሶዎች ቢተከሉም እስከ አሁን ድረስ ለውጥ ባለመደርጉ ምክንያት የአከባቢው ነዋሪዎች ሚያዝያ 12 / 2006 ዓ/ም 6 የኤሌክትሪክ ሞሶሶዎች  ነቅለው በመጣል በህውሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት አንታለልም ሲሉ ብሶታቸውን እያሰሙ እንዳሉ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አመለከተ።