Monday, April 28, 2014

በትግራይ ክልል የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ለአካባቢው ህዝብ ባላመነበት መንገድ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያስገደዱት መሆናቸው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።




በመረጃው መሰረት በኲሓ ከተማ የሚገኙ የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ለአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ገንዘብ እንዲያዋጣ ቢያስገድዱትም ህዝቡ ግን ቀደም ሲል ለመሰረተ ልማት ብለን ያሰባሰብነው ገንዘብ ለግል ጥቅማችሁ ስላዋላችሁት ዛሬ ይሁን ነገ የምናዋጣው ገንዘብ የለንም ሲል እንደተቃወመው ተገለፀ።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ አስተዳዳሪዎቹ ሃሳባቸውን በመለወጥ የምታዋጡት ገንዘብ በከተማችን ውስጥ ለሚሰራው መንገድና ለኮብልስተን ስራ የሚውል ነው ቢልዋቸውም ነዋሪዎቹ ግን ከአሁን ጀምሮ ሰርተን ልጆቻችን ለማሳደግ እንጂ እናንተን ለመጥቀም ብለን የምንሰጠው ሳንቲም የለንም በማለት በአስተዳዳሪዎቹ ለቀረበው ሃሳብ እንደተቃወሙት የደረሰን መረጃ አመልክተዋል።
     በመጨረሻ። የእንደርታ ህዝብ ባሳየው የእንቢተኛነት መልስ ስጋት ላይ የወደቁ የስርአቱ ካድሬዎች ህዝቡን ሰብስበው ለምንድነው የመንግስትን ትእዛዝ የማታከብሩት በመካከላችሁ ጠላት ገብተዋል በማለት እያስፈራርዋቸው እንደሆኑ። ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል።