Monday, April 28, 2014

በሰሜን እዝ የሚገኙ የወያኔ ኢህአዴግ ወታደሮች ስርዓቱን እንደ አዲስ ለማገልገል ፈርሙ በመባለቸው ምክንያት ተቃውሞአቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ሊታወቅ ተችሏል።



እነዚህ በሰሜን እዝ የሚገኙ የስርዓቱ ወታደሮች ለ7ትና ለ10 አመታት  ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በወታደር ቤት የነበረን አገልግሎት እዚህ ላይ አብቅትዋል በማለት የስንብት ወረቀት እንዲሰጣቸው ለሚመለከታቸው የሰራዊቱ አዛዦች ደብዳቤ ያስገቡ ቢሆኑም የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች መጀመርያ የገቡላቸውን ቃል ወደጎን በመተው እንዳዲስ በወታደር ቤት ስራ ላይ እንዲቀጥሉ ፈርሙ ስላሉዋቸው በአባላቱ ውስጥ ሃያል ተቃውሞና ግርግር አስነስቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
     መረጃው በማስከተል እነዚህ ወታደሮች በ1991 እና በ1992 ዓ.ም ወደ ውትድርና የገቡ እንደሆኑና ለ7ት አመት ብቻ ተብለው እንደፈረሙ የገለፁ ቢሆኑም የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮነኖች ግን የስንብት ወረቀት እንዲሰጣቸው ለጠየቁና እንዳዲስ አንፈርምም ላሉ ወታደሮች ሰብስበው። እናንተን ወደ ሰላም አስከባሪነት እንሰዳችሁአለን ብቻ እንዳዲስ ለማገልገል ፈርሙ እያሉ በማይተገበር ቃላት ሊያታልልዋቸው በሞኮሩበት ጊዜ ለዚህ አደናጋሪና መሰሪ የሆነውን የአመራሮቻቸውን ንግግር እንደተቃዎሙት መረጃው አስታውቋል።
     መረጃው በመጨረሻ መንግስት ለአዳዲስ ምልምል ወታደሮች ለ7ት አመት ብቻ ነው የምታገለግሉት እያለ: ተግባር ላይ ለማያውለው ነገር እንዲፈርሙ ማድረጉ መሰረታዊ ስህተት ነው በማለት በመንግስት ባለስልጣናትና በሰራዊቱ መኮነኖች መካከል ሊፈታ የማይችል ችግር ተፈጥሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው በዚህም የተነሳ የሰሜን እዝ ሓላፊ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ ለሁሉም የሰሜን እዝ የሰራዊት አባላት መንግስት መሰረታዊ የሆነ መፍትሄ እስኪያመጣ ድረስ ማነኛውም ወታደር ከአሃዱ ወደ ቤተሰቡ ይሁን ወደ ሌላ ስፍራ መንቀሳቀስ የለበትም የሚል አዲስ መምርያ አውርዶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።