Sunday, April 27, 2014

በምዕራብ ትግራይ ዞን የአዲጎሹ ከተማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤታቸው በከተማ አስተዳዳሪዎች ትዕዛዝ እየፈረሰ መሆኑን ከኣካባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።


በመረጃው መሰረት በምዕራብ ትግራይ ዞን አዲ ጎሹ ከተማ የሚኖሩ ዜጎቻችን ለረጅም ጊዜያት ሲጠቀሙበት የነበሩ ከ30 በላይ መኖሪያ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን አሁንም ከ20 በላይ የሚሆኑ ቤቶች በከተማው አስተዳዳሪ ትዕዛዝ እንደሚፈርሱ መገለፁንና በዚህ ምክንያትም የመኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች በበረሃ ተጥለው በፀሓይና በውርጭ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
    መረጃው ጨምሮም ከብዙ አመታት በፊት በህጋዊ መንገድ በተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉልበትና መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው በመስራት ለብዙ አመታት የኖሩበትን ቤት ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና የካሳ ክፍያ እንደፈረሰ ጠቅሶ ህጋዊ አይደለም ብለው የተቃወሙ ዜጎችን ደግሞ ወደ ሑመራ ከተማ በመውሰድ አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሆኑና ከእነዚህም መካከል-ማሞ አዶጉ፥ ገብረ መስቀል ጉዑሽና ሌሎችም እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።