Tuesday, April 8, 2014

የኢህአዴግ ስርአት ወታደራዊ ሃላፊዎች በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ባለው በደል ተማርረው ለስራ የተሰጣቸውን ገንዘብ ይዘዉት እየሸሹ መሆናቸው ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



ወታደራዊ አማራሮቹ በመከላክያ ሰራዊት ዉስጥ ያለ አድልዎ ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ በመምጣቱ ምክንያት ለስራ የተሰጣቸዉን ገንዘብ’ና ንብረት ይዘዉት እየጠፉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው እርምጃውን ከወሰዱት ሰዎች ደግሞ በ24 ክፍለ ጦር የኢንዶክትሪነይሽን`ና ኦፕሬሽን ሃላፊ የሆነ ሻምበል ደረጀ ቀልቤሳ የተባለ ግለሰብ እንደሚገኝበት ተገለፀ።
    ሰላም አስከባሪ ተብለው ወደ ዳርፉር የሚላኩ ወታደሮች በአድልዎ እንጂ በትክክለኛ መስፈርት የተመለመሉ አይደሉም በማለት የገለፀዉ ሻምበል ደረጀ ለስራ ተብሎ የተሰጠውን የክፍለጦሩ 32 ሺ ብር ይዞ በመጋቢት 4 /2006 ዓ.ም እንደተሰወረ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል።
    ገንዘቡን ይዞ የተሰወረዉን ሻንበል ለመያዝ የተሰማሩ የአስራ አለቃ ሸንኩት ኦኬሎና ምክትል የአስራ-አለቃ ተስፋየ በለጠ ሑመራ ከተማ ውስጥ ሲፈልጉት እንደሰነበቱና ማግኘት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችለዋል።