Tuesday, April 8, 2014

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት ባለ ስልጣናት በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ዳርፉር ለሚሄዱ ወትሃደሮች በሚያደርጉት ምልመላ ላይ ጥቅምን ማእከል አድርገው ስለሚያካሄዱት በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ መከፋፈል መፈጠሩ ተገለፀ።



     ከሰሜን እዝ 33 ክ/ጦር ውስጥ በየካቲት 10/ 2006 ዓ/ም በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ዳርፉር ለሚሄዱ በተካሄደው ምልመላ ላይ አብዛኛዎቹ አዲስ እንደሆኑና ምልመላውም በቤተሰባዊ፤ አካባካባቢያዊና በጥቅም የተፈፀ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
      አዲስ ወተሃደሮች ከነባሩ የሰራዊቱ አባል በፊት ወደ ሰላም ማስከበር ስራ እንዲመለመሉ የሚፈቅድ ህግ የሌለ ቢሆንም የክፍለ-ጦሩ አዛዦች ግን እንዲመለመሉ ለማይፈልጉዋቸው ያገለገሉ አባላት ችግሮች እንዳልዋቸው አስመስለው በማግለል በነሱ ምትክ ምንም አይነት ተሞኩሮ ለሌላቸው አዲስ ምልምሎች ማሰማራታቸው የአመራሮቹ ብልሹ አሰራር የሚያሳይ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።
     ተገቢነት በጎደሎው አሰራር ሰላም አስከባሪ ተብለው የተላኩት የሰራዊቱ አባላት ከሚያገኙት ገቢ መልምለው ለሚልኩዋቸው ሃላፊወች እንዲከፍሉዋቸው በማሰብ ተስማምቶው እንደሚፈፅሙት የገለፀው መረጃው ከ1991ዓ/ም ጀምሮው በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያገለገሉና ያለ አግባብ የተመለመሉ የሰራዊቱ አባላት  የጎሪጥ እየተያዩ እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።
      ይህ በእንዲህ እንዳለ በሸራሮ ግንባር ከሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የድስፒሊን ችግር አላቹህ ተብሎው በቅርብ ቀን የተባረሩት በርከት ያሉ ወተሃደሮች ያለምንም የገንዘብና የትራንስፖርት ድጋፍ በመሸኘታቸው ምክንያት የሚትኙበት ቦታ አጥተው በሸራሮ ከተማ መንገዶችና አውቶብስ መናሃርያ ላይ ተጥለው እያደሩ መሆናቸው የተገኘው መረጃ አመልክተዋል።