Tuesday, April 8, 2014

ሑመራ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ሆስፒታል ለስሙ እንጂ በውስጡ ምንም አይነት የመድሓኒት አቅርቦት የለውም ሲሉ የአካባቢው ህብረተሰብ በ18/07/ 2006 ዓ.ም አቤቱታቸውን አሰሙ።



የሑመራ ከተማና የአካባቢው ህብረተሰብ ካላዛር በተባለ በሽታ ተይዘው በመሰቃየት ላይ ለሚገኙ ዜጎቻችን የሆስፒታሉ ባለስልጣናት እኛ ልናክማችሁ አቅሙ ስለሌለን መቐለ ከተማ ወደ ሚገኘው አይደር ሆስፒታል ሄዳችሁ መታከም ትችላላችሁ እያሉ ወደ መጡበት እንደሚመልስዋቸው የገለፀው ይሀው መረጃ በዚህ የተነሳም በቅርብ ግዜ በሞቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በበሽታው ተለክፈው ቤታቸው ውስጥ ሁነው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ለበሽታው ሰለባ የሆኑትን መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አመልከተ።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ- የአካባቢው ህብረተሰብ ሃብታም ወደ ፈለገበት ሂዶ በገንዘቡ ሊታከም ይችላል አቅም የሌለውና ድሓው ህብረተሰብ ግን እንዴት አድርጎ መቐለ ሂዶ ሊታከም ይችላል?
Ø ለምንድን ነው የህዝብ ችግር ሊፈታ የማይችለው?
Ø እስከመቼ ነው መቐለ ህክምና እየሄድን የምንታከመው?
መንግስት ለህብረተሰባችን ህይወት በፍፁም የማያስብና ሃላፊነት የሚባል ነገር የሌለው ነው እያሉ በስርዓቱ ላይ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል።