Tuesday, April 8, 2014

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በቂ የማህበራዊ አቅርቦት ሊያገኙ ባለመቻላቸው ምክንያት በከባድ ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት በዩኒቨርሲቲው በቂ የሆነ የማህበራዊ አቅርቦት ባለመኖሩ ተማሪዎቹ በርሃብ እየተስቃዩና ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጠው በየቀኑ ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸው የታዘቡት በርከት ያሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለህይወታቸው ደህንነት ሲሉ ለአመታት የደከሙለትንና የሚወዱት ትምህርታቸውን ትተው ወደ ቤታቸው ለመሄድ እየተገደዱ እንዳሉ ታወቀ።
   የማህበራዊው አቅርቦት እጥረት ዋነኛው ምክንያት፤ የዩኒቨርሲቲው ግዢ ክፍል ሃላፊው፤ በዩኒቨርሲቲው  መምህር የሆኑት ሰመረ ዮውሃንስና መምህር ቴድሮስ ሃይሉ የተባሉት ግለሰቦች ለማህበራዊ አቅርቦት መግዣ እንዲውል ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት መረጃው ጨምሮ አስረድትዋል።
  በማህበራዊ እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን ኳቛረጡት ተማሪዎች  ለመጥቀስ ያክል፣
1.  አፈወርቂ ታመነ ነዋሪነቱ በፀለምቲ ወረዳ፤
2.  ደሴ አለባቸው ነዋሪነቱ በሰሜን ጎንደር የሆነ ታምሞ ህክምና ከገባ በኋላ በዛው አድርጎ ወደ ትውልድ ቦታው የሄደውና ሌሎች  እንደሚገኙባቸውና በዩኒቨርሲቲው ግቤ ውስጥ በፅዳትና  የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት እጥረት ተማሪዎቹ እየተቸገሩ መሆናቸው  መረጃው አክሎ ገልፆዋል።