Thursday, May 8, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ሃፍተ ማሪያም ቀበሌ ውስጥ በርከት ያሉ ዜጎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ አልተሳተፋችሁም ተብለው በእስር ቤት ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት የሃፍተ ማርያም ነዋሪ የሆኑ ዜጎቻችን  በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ላይ አልተሳተፋችሁም በሚል ምክንያት ከየካቲት 2006 ዓ.ም ጀምረው በእስር ቤት ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ያለምንም ወንጀል በእስር ቤት እየማቀቁ ከሚገኙት ውስጥም አቶ ተስፋሚኪኤል ግርማይ፤ አቶ ገብረግዛብሄር ገብሩና ኤሎችም እንደሚገኙባቸው ታወቀ።
   መረጃው በማስከተልም  እነዚህ ንፁሃን ዜጎቻችን ቀስቃሽ የሚል ስም ተስጠተውና  በሐሰት  ተከሰው  በእስር ቤት እንዲሰቃዩ ካደረጉት የስርአቱ ተላላኪ ካድሬዎች  መካከል አቶ ኪዳነ ተስፋ ማርያምና ባልደረቦቹ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
   እነዚህ በስቃይ የሚገኙ ወገኖች የገጠማቸው ችግር እንዲፈታላቸውና ድኻ ቤተሰቦቻችውን ሰርተው ለማስተዳደር ሲሉ  ከእስር ቤቱ አውጡን የሚል አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ አካል እንዳላገኙ ከእስር ቤቱ የወጣ መረጃ አመለከተ።