Thursday, May 1, 2014

በትግራይ ሴሜናዊ ምዕራባዊ ዞን ዓዲ ሃገራይ ከተማ በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ልባቸው የቆሰለ ዜጎቻችን ሚያዚያ 12/2006 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ የስርዓቱን ወታደራዊ መኪና ከነንብርትዋ እንደወደመች ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በተገኘው መረጃ መሰረት በወያኔ ስርዓት ወታደሮች ተግባር ትግስታቸው የተሟጠጠ የከተመዋ ነዋሪዎች በዓዲ ሃገራይ ከተማ ብሄራዊ ሆቴል አካባቢ ቁማ ለነበርችው ኦራል ወታደራዊት መኪና ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከጥቅም ውጭ መሆንዋ ለማወቅ ተችልዋ።
   ከከተማዋ ሳንወጣ ሽራሮ ምግብ ቤት ፊት ለፊት ቁማ ለነበረችው የመከላከያ ሰራዊት የውሃ ማማላለሻ ቦቴ መኪና የያዘችውን ውሃ ያፈሰሱት ሲሆን ይህ ተግባርም በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ የሚያመላክት  መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።