Thursday, May 1, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የሽሬ ከተማ ወጣቶች ሰርተው ያጠራቀሙትን ገንዘብ በከተማዋ የፖሊስ አዛዦች እየተቀሙ እየታሰሩ መሆናቸው ከከተማው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



   የሽሬ ከተማ ወጣቶች በድንጋይ ማንጠፍ ስራ ተሰማርተው ላባቸውን አፍስሰው ያጠራቀሙትን ገንዘብ የሽሬ ከተማ ፖሊስ አዛዦች አካፍሉን በማለት ሲያስገደዷቸው እምቢ ስላሉ ብቻ ሰርቃችኋል በማለት ገንዘባቸውን በመቀማት እያሰሯቸው መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
  ገንዘባችንን አንሰጥም በማለታቸው ምክንያት ሚያዝያ 12/2006 ዓ/ም ከታሰሩት ወገኖች መካከል ባሻይ ታረቀ፤ ግደይ አለምሰገድ፤ መኮነን ታፈረ፤ ጌታቸው አለምፀሓይና ሌሎችም እንደሆኑ የገለፀው መረጃው በማንገላታት ተግባር የተሰማሩ የፖሊስ አዛዦች ደግሞ ኮማንደር ኪዳኔና ጎሹ የተባሉ ሲሆኑ ወንጀል ላልፈፀሙ ሰዎች በጉልበታቸው ሰርተው ለሚኖሩ ወጣቶች በፋሲካ በዓል ወስደው በማሰርና የዋስ መብታቸውን እንደከልክለቸው ታውቋል።
  በተመሳሳይ የትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ሽሬ ከተማ መምጣታቸውን ያወቁት ከ140 በላይ የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች መሬትን የሚመለከት ጥያቄ ለባለስልጣኖቹ ለማቅረብ ወደ ሽሬ ከተማ መሄዳቸውን ከከተማው የደረሰን መረጃ አመለከተ።