Thursday, May 1, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽሬ ከተማ ሚያዚያ 14/2006 ዓ.ም በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ የተመራው ስብሰባ ያለ ፍሬ መበተኑ ተገለፀ።



በተገኘው መረጃ መሰረት አባይ ወልዱ፤ አባይ ፀሃየ፤ ዶክተር ደብረፅዮን፤ ቅዱሳን ነጋና ሌሎችም የሚገኙበት ለሽሬ ከተማ ነዋሪዎች ለማወያየት በተጠራው ስብሰባ ላይ ብዛት ያለው የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ በስብሰባው እንዳልተሳተፈ የገለፀው መረጃው በስብሰባው ላይ የተገኙት አንዳንድ የስርዓቱ ደጋፊም ቢሆኑ የነበረውን መድረክ ረግጠውት እንደወጡ ለማወቅ ተችልዋል።
    በማስከተልም የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች በነበርው ስብሰባ ላይ ተራ በተራ በመነሳት እንደገለፁት ስርዓቱ ወደ ግለኝነት ስለ ተቀየረና እናተም የሱ አካል ስለሆናችሁ ከኛ ጋር የሚያገናኝ ነገር የላችሁም እኛም የናንተ አጃቢ አይደልንም በማለት የተጠራውን ስብሰባ አቋርጠውት የሄዱ ሲሆን ከነዚህም የተወሰኑትን ለመግለጽ ያክል አቶ ሳልህ ዓብደላ፤ አቶ ተስፋየ፤ አቶ ገብረኪዳን ሐኪም፤ ዶ/ር ማዓሾና ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ እንደሚገኙባቸው መረጃው አስታውቋል።
    ባለ-ስልጣኖችም በህዝቡ ተቃውሞ በመደንገጣቸው። ስብሰባውን ረግጦ ለሄደው ህዝብ ለመመለስ ሲሉ ከበደልን እናስተካክላለን በማለት ለማረጋጋት የሞከሩ ቢሆንም የሽሬ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ግን ሊሰማቸው እንዳልቻለና በውይይቱ አንካፈልም በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን። ከነዚህም ውስጥ የቀድሞው የህ.ወ.ሃ.ት አባል የነበረ አቶ ግርማይ አስገዶምና በርከት ያሉ ዜጎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።