Thursday, May 1, 2014

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለ-ስልጣኖች ለስርዓቱ ታማኝ የሆኑትን ካድሬዎችና የፖሊስ አዛዦች በክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን አዳራሽ ሰብስበው ባደረጉት ንግግር አንዳንድ የፖሊስ አዛዦች ለቀረበው ሃሳብ በመቃዎም የነበረውን የውይይት መድረክ ረግጠውት እንደውጡ በውይይቱ ላይ ተካፋይ የነበሩ ምንጮቻችን ገለፁ።



በመረጃው መሰረት እየተካሄደ በነበረው ስብሰባ ላይ ፖሊስ ተተኳሽ ነገሮችን በመሽጥ፤ ጉቦ በመቀበል፤ ሰዎችን በኮንትሮባንድ ወደጎረቤት ሃገር በማሸጋገር ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል ብለው በስብሰባው ላይ ተካፋይ የነበሩ አንዳንድ ወገኖች በሚገመግሙበት ግዜ ወዲ ሻምበል በሚል ቅጥያ ስም የሚታወቀው ዘአማኔል የተባለው የትግራይ ክልል የፖሊስ ሃላፊ ስብሰባውን ረግጦት እንደወጣ ሊታወቅ ተችሏል።
    በተመሳሳይ ከተሳታፊዎቹ አንዱ የሆነው የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገብረኪዳን ወዲ ሽራሮ በበኩሉ ህዝብ ሰብስባችሁ ክ-ከምታዋርዱን ለብቻችን ለምን አትገመግሙንም በማለት ስብሰባውን አቋርጦት እንደወጣ መረጃው አክሎ አስረድቷል።