Thursday, May 1, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ተቃዋሚ አባላት ሚያዝያ 16/ 2006 ዓ/ም 5000 ለሚደርሱ አባሎቹ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ የድርጅቱ አባላት በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት እንደታሰሩ ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



መረጃው በማስከተል እነዚህ የሰማያዊ ፓርቲ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት ሚያዝያ 16/2006 ዓ/ም በሳሪስ፤ ጎተራ፤ በተክለ-ኃይማኖትና በአምቦ በርከት ላለ ህዝብ ቅስቀሳ እንዳካሄደ በመግለፅ የከተማዋ የፌዴራል ፖሊስ ግን የህዝብን መብት በመንፈግ ብዙ የተቃዋሚ አባላትን በዱላ እየደበደቡ ወደ እስር ቤት ወስደው እንዳጎርውቸውና ከታሰሩት አባላት ውስጥም ኢንጂነር ካሱ ኢላላ የተባለውን  ወጣት ከአምቦ አካባቢ ጠልፈው በመውሰድ የት እንዳደረሱት እስከአሁን የታወቀ ነገር እንደሌለ ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በተቃዋሚ ድርጅት አባላቶች ላይ በስልጣን ባለው መንግስት እየተፈፀመባቸው ያለው በደልና ግፍ የአንድ አምባገነናዊ ስርዓት ውድቀትን የሚያሳይ ምልክት ነው ሲሉ አንዳንድ ወገኖች በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።