Sunday, May 4, 2014

በጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝና በሃገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ጄነራሎች መካከል ከባድ ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



    በመረጃው መሰረት ሚያዝያ 14/ 2006 ዓ/ም ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ በመሩት የጄነራሎች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስን የሚተካ ማን ይሁን በሚል  አጀንዳ ላይ እንደነበረና። በዚህም ጉዳይ መስማማት ባለመቻላቸው ምክንያት በመካከላቸው ክፍፍልና ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃለማርያም ደሳለኝ ስልጣኑን ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ይረከበው በማለቱ ቅር የተሰኙ ሌሎች ተሳታፊዎች ግን ሌተናል ጄነራል  ሰዓረ መኮነን ወይም ሌተናል ጄነራል ዮውሃንስ ገብረመስቀል መሆን አለባቸው ብለው ላቀረቡት ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለ ተቃወሙት ስብሰባው ያለ ስምምነት እንደተበተነ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    በጠቅላይ ሚኒስተሩና በስርአቱ ጀኔራሎች ያለው ያለመስማማት ወገናዊነት የተጠናወተው እንጂ ለሀገርና ለህዝብ በማሰብ የተደረገ ክርክር እንዳልሆነ አንዳንድ የሰራዊቱ የበላይ አዛዦች ጉዳዩን አስመልክተው እየተናገሩበት መሆኑንና በአሁኑ ግዜ ሌተናል ጄነራል  አበባው ታደሰ ባጋጠመው የጤና ችግር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በህክምና ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።