Sunday, May 4, 2014

በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መከላከያ ሰራዊት የበላይ አዛዦች ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በኮሎኔልነት ማዕረግ የሚገኙባቸው የሰራዊቱ አባላት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ መሆናቸውን ከመከላከያ ሸልኮ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



እነዚህ በሚያዝያ 2/2006ዓ/ም የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡት የስርአቱ የበላይ መኮንኖች ኮሎኔል ዓንደንክኤል ወልደማርያም የትግራይ ምእራባዊ ዞን ተወላጅ፤ ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረዝጊአብሄር የትግራይ ማእከላዊ ዞን ተወላጅ እንደሆኑ የገለፀው መረጃው በስርአቱ የተሰጣቸው መልስ ግን። ባስነሳችሁት ጥያቄ ምክንያት ሌሎች የሰራዊቱ አባላት የስንብት ጥያቄ እያስነሱ ነው! አታነሳስቡን መንግስት የሚሰጣችሁን ደሞዝ አርፋችሁ ብሉ የሚል የማስፈራርያ መልስ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሾልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ግዜ በሁሉም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ውስጥ የ7 አመት አገልግሎታችን ስላበቃ ወደ ትውልድ ቦታችን አሰናብቱን የሚሉ ጥያቄዎች በሰፊው እየተነሳ መሆኑንና በዚህም ምክንያት ጥያቄ ላስነሱት የሰራዊቱ አባላት አነሳሾች ተብለው እየተቀጡና እየታሰሩ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።