Monday, June 16, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ለስኳር ፋብሪካ ተብሎ እየተሰራ ባለው ፖሮጀክት ውስጥ ያሉ ሃላፊዎች የህዝብንና የሃገርን ንብረት እየዘረፉ መሆናቸው ታወቀ።



ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት ግንበት 28/2006 ዓ/ም በወልቃይት ወረዳ እየተሰራ ባለው የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለፕሮጀክቱ አመራሮች የህዝብንና የሃገርን ሃብት እየዘረፋችሁ ናችሁ ብለው በስብሰባው ላይ በመገምገማቸው ምክንያት ከድርጅቱ እንደአባረሯቸው ለማወቅ ተችሏል።
       በሃላፊዎቻቸው ላይ የታየ ችግር በመገምገማቻው ብቻ ከተባረሩት ሰራተኞች መካከልም…
1.  አለማዮህ ሃይለ (በወዲ ሸራሮ ቅጥያ ስም ሚታወቀው)
2.  ሃፍቱ የተባለ (በወዲ ራያ ቅጥያ ስም  የሚታቀውና) ሌሎችም እንደሚገኙባቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።