ያገራችን ሰማእታት በከፈሉት
የመስዋዕትነት መጠንና ባሳዩት አስደናቂ ጀግንነት ሁሌ በታሪክ መዝገብ እየተዘከረ ሊኖሩ የሚገባው ቢሆንም የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ግን
በጀግኖቹ ታሪክ ግድ የሌላቸውና የማይሰማቸው የወያኔ ኢህአዴግ መሪዎች ለማስመሰል ሲሉ የገዛ ህዝባቸውን ለማደናገር በአላት እየደረደሩ
ህዝቡን በማስገደድ እንዲጨፍሩና እስክስታ እንዲመታ በማድረግ ለሰማእታት ክብር በማይገልፅና በሚያዋርድ መንገድ በዓሉን ሲያካሂዱት
ይስተዋላሉ፣፣
የአገራችን ጀግኖች ሰማእታት ከውጭ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን አገራቸው ውስጥ
ከተፈጠሩ ፀረ ህዝብ ስርአቶች በተደረገው አውደ ውጊያም ታሪክ ሰንደው አልፈዋል፣ መስፍናዊ የሃይለስላሴና የደርግ ስርአት ለማስወገድ
በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግልም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጀግኖች ህይወታቸውን ሲከፍሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አካላቸው ጎድሏል።
የደርግን ስርአት ለመደምሰስ ተብሎ በተካሄደው መራራ ትግል በተለይ በህዝባዊ
ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪነት የተካሄደው የትግራይ ህዝብ ትግል ላቅ ያለ ጀግንነት የተፈፀመበት መድረክ እንደነበረና በመጨረሻም
ፀረ ህዝብ የደርግ ስርአት ተገርስሶ ከስልጣን ተወግዶ የኢትዮጵያ ህዝብ ትንሳኤ እንደተረጋገጠ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጋሪ የሚያስፈልገው
አይደለም።
አጠቃላይ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ጀግኖች ሰማእታት
ታግለው በደማቸውና በመስዋእትነታቸው ያስገኙትን የስርአት ለውጥ የራሳቸውንና የህዝባቸውን ጥቅም ለማረጋገጥ አላስቻለም፣ በትግራይ
ደረጃ ብቻ የሚከበረውን ሰኔ 15 የሰማዕታት በዓል ህዝቡን ለማደናገርና ሰማእታትን የሚያስታውስ ስርዓት እንዳለ ለማስመሰል ተብሎ
በየአመቱ የሚከበር እንጂ የሰማእታትን አደራና ክብር ለማስጠበቅና የተሰውትን ቤተሰብ ለመጥቀም ተብሎ የሚደረግ አይደለም።
ሰኔ 15/1980 ዓ/ም በሃውዜን ከተማ በጠራራ ፀሃይ ላይ ከ2500 በላይ
ንፁሃን ወገኖቻችን በፋሽስታዊ የደርግ ስርአት ቀጥተኛ ትእዛዝ ሂወታቸውን ሲያጡ የትግራይን ህዝብ ልብ በሃዘን የተዋጠበት ነገር
ግን ህዝቡ በትግል ወቅት ፈታኝ መድረኮች እንደሚያጋጥሙ ከትግሉ መጀመርያ ጀምሮ ስላመነበት። ከጠላቶቹ ለሚሰነዘሩ ፋሽታዊ ጥቃቶች
እንደ አመጣጣቸው እያስተናገደ ህዝባዊ ትግሉን እንደሚያስቀጥለው በማመን በንፁሃኑ ህዝቦች ላይ የተፈፀመውን በደል ለመበቀልና የጠላቶቹን
እድሜ ለማሳጠር ከወራቶች ቆይታ በኋላ በይዘቱና በትልቅነቱ ወደር ባልነበረውና የስርአቱ ዋነኛው የደም ስር በሆነው የ 604ኛ ኮር የጠላት ሰራዊት ላይ ጥቃት ፈፅሞ ድልን በመቀናጀቱ
ምክንያት መላውን የሃገራችን ክፍል ለመቆጣጠር ይደረግ በነበረው ጉዞ ላይ ወደ ድል አፋፍ እንዲቀራረብ ምክንያት ሆኖ እንደነበር
ሁሉም ዜጋ ያስታውሰዋል።
ታድያ ይህ በዘመናዊ ጦር መሳርያዎች፤ መድፎች፤ ታንኮችና የጦር ተዋጊ
አውረፕላኖች ታግዞ እየተዋጋ የነበረውን የጠላት ሃይል ድባቅ መትተው ድል ለተቀናጁ በሂወት ያሉትና በክብር ያለፉትን
ሰማዕታትና አርበኞቻችን ለምን ይሆን በስልጣን ላይ ከተወጣ በኋላ
ላለፈው ጀግንነትና ታሪክ ሰሪነትን አስታውሰህ የሚገባቸውን ድጋፍና ክብር እንዲደረግላቸው ያልተቻለው።
የትግራይ
ህዝብ አይደለም ለሰኔ 15 በደርግ ባለስልጣኖች ትእዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ቀን ጥሩ ስነ-ምግባርና
ህብረተሰብአዊ ተቀባይነት ላለው አብሮ አደግ ጎረቤትም ቢሆን፣ በልቡ እያሰበና ህይወቱን ያለፈበት ቀን እያስታወሰ የሚዘክር የዋህ
ህዝብ ነው፣፣
የተከበርክ
የትግራይ ህዝብ ሆይ የወያኔ ኢህአዴግ ሽማምንቶች የሰማእታት ደምና ስጋ እየጠጡና እያመነዠኩ ወደ ስልጣን ሊወጡ ባበቃቸው ታጋይና
ህዝብ ስም እየነገዱ፣ አሁንም እንደለመዱት ለማስመሰልና፣ ወደዚህ
ላበቁን ሰማእታቶች እንዘክራቸው ማለታቸው አይቀሬ ነውና የበአሉ ስነስርአት ለሰማእታት የማይወክልና የነሱ መስዋእትነት በህዝቡና
በተሰው ቤተሰቦች ላይ ያስገኘው ለውጥ እንደሌለ በማመን የጀግኖች ደምና አጥንት እንዳይራከስና ክቡር መስዋእትነታቸው ለዘለአለም
ተከብሮና ተዘክሮ እንዲኖር ከተፈለገ አሁንም በጠላቶችህ ላይ እያካሄድከው ላለው ትግል ማጠናከር ይገባሃል፣፣