የመቐለ ከተማ ህዝብ ሰኔ 27 /2006 ዓ/ም ወደ ጅንአድ ፅህፈት ቤት በመሄድ
በዘይት እጥረት ጉዳይ ምሬቱን በገለፀበት ጊዜ የጅንአድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ የኑስ መሃመድ “አዎ እውነታችሁን ነው በተለይ ከሰኔ
ወር 2006 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ የምግብ ዘይትና ሌሎች ነገሮች እጥረት እንዳጋጠመ ይታወቃል”ሲል የአዞ እንባ እያነባ የማተለያ ምላሽ መስጠቱ
ለማወቅ ተችሏል።
ከከተማዋ በተገኘው መረጃ መሰረት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዝቅተኛና
መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎች ማህበራዊ ኑሮአቸውን ለማስተካከል በድጎማ እያሟላሁ ነው ቢልም እንኳን እንደ ዘይት፤ ፍርኖ ዱቄት፤
ስኳርና የመሳሰሉ መሰረታዊ ሸቀጦች በህዝብ ስም እየተገዙ ለስርዓቱ ተላላኪ ለሆኑት የጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት ሃላፊዎች የኪስ
መሙያ እየዋለ እንዳለ ይታወቃል።
መረጃው በማስከተልም በተለይ ከ40 ቀናት በፊት ጀምሮ እስከ አሁን በመቐለ
ከተማ የምግብ ዘይት ጠቅልሎ ከገበያ መጥፋቱን የገለጸው መረጃው የአስተዳደር አከፋፋይ ተብለው የተቀመጡ ነጋዴዎች ግን ለህዝብ ተብሎ
የተረከቡትን የፓልም ዘይት ደብቀው ቆይተው አሁን በእጥፍ ዋጋ ማለትም ለ3 ሊትር ዘይት ከ90 እስከ 100 ብር እየሸጡ እንደሆኑ
የታዘቡት የአዲ ሃቂ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ብሶታቸው እየገለፁ መሆናቸውን አስረድተዋል።