በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በመቐለ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች በገዥው የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ከአቅማቸው
በላይ ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉበት ዋነኛ ምክንያት፤ በዚህ ህጋዊ ባልሆነ ግብር ተሸማቀው ከተቃዋሚ ድርጅቶች አባልነት እንዲወጡ
የታቀደ መሆኑን ለችግሩ ሰለባ የሆኑትን መሰረት በማድረግ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስታወቀ፣
እኒህ ነጋዴዎች ለስርዓቱ ካድሬዎች ይህ
እየጠየቃችሁን ያላችሁት ግብር ከአቅማችን በላይ ነው እኛን አይመጥነንም በማለት፤ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተሰማቸውን
አቤቱታ ቢያቀርቡም፤ የተጠየቃችሁት ግብር አልበዛባችሁም ይመጥናችኋል መክፈል አለባችሁ የሚል ሃላፊነት የጎደለው መልስ ሰጥተው እንደመለሷቸው
ለማወቅ ተችሏል፣