Thursday, May 15, 2014

በኢትዮጵያ ፀረ ወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተጀምሮ ያለውን ሰለማዊ ሰልፍ በአዲስ መልኩ ተጠናክሮ ሚያዝያ 28/2006 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ መቱ ከተማ እየቀጠለ እንዳለ ታወቀ።



ምንጮቻችን ከቦታው እንዳስታወቁት ፀረ ወያኔ ኢ.ህ,አ.ዴ.ግ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀጠለ እንዳለ ከገለፀ በኋላ በተለይም ሚያዝያ 28/2006 ዓ/ም በኦሮሚያ የምዕራብ ወለጋ መቱ ከተማ ነዋሪዎች ፀረ ወያኔ ስርዓት ሰለማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችለዋል።
በመቱ ከተማ ነዋሪዎች የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ያሰጋቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት ከአዲስ አበባ የተላኩት የፌደራል ፖሊስ በከተማዋ ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት 4 ንጹሃን ዜጎች ገድለው ከ12 በላይ  እንዳቆስሉ  የገለፀው መረጃው በስርዓቱ የፀጥታ ሃይሎች ጥይት ተገድለው ህይወታቸው ካለፉ ንፁሃን ወጎኖቻችን…..
1.     በቀለ ድጎማ የተባለው የ12ተኛክፍልተማሪ
2.     አለማዩ እዴሳ በንግድ ስራ የሚተዳደር
3.     ፈይሳ አለማ ተማሪ
4.     መምህር ሓሰን አህመድ የተባሉትና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል ፣