ምንጮች በላኩት መረጃ መሰረት ለበላይ አመራሮች እየተሰጠ የቆየውና አሁንም
ለበታች የመንግስት አመራሮች እየቀጠለ ያለው ስብሰባ የውይይቱ ርእስም የአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርመሽን አፈፃፀም የተመለከተ
እንደሆነ ቢነገርም በተግባር ግን ዋናው ማነጋገገርያ ርእስ ሆኖ የቀረበው ቀጣይ 2007 ዓ.ም በሚካሄደው ምርጫ ላይ ያተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏዋል።
የስብሰባው መሪዎች ማንኛውም የስብሰባው ተካፋይ የሆነው የመንግስት ሰራተኛ።
ለህወሃት ኢህአዴግ ድርጅት እንዲመረጥ ለማድረግ የተቻለውን ያህል መንቀሳቀስ እንዳለበትና ይህንንም ለማሳካት ካሁን ጀምሮ ምርጫ
እስከሚካሄድበት ግዜ ማንኛውም ሰው ለተቃዋሚዎች እንዳይመርጥና እንዳይደግፍ ቅስቀሳ በማድረግ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ተስፋ ማሳጣት፤
በምርጫው ሰበብ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይነሳ ክትትል ማድረግ ያገኙትን መረጃ ወድያውኑ ወደ ሚመለከታቸው አካላት እንዲያሳውቁ
የሚል ጥብቅ መመሪያ እየሰጧቸው እንደሆነ የተገኘው መረጃ ገልጿል።
በተመሳሳይ በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የሚገኙ በመንግስት ፅ/ቤት የሚሰሩ
ሃላፊዎችና ሰራተኞች 2007 ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ ላይ አስመልክቶ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
ይህ በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን በሚገኙ የመንግስት አመራሮችና የበታች
ሰራተኞች እየተካሄደ ያለውን ስብሰባ እንዲመሩ የተላኩት የስርአቱ ካድሬዎች ስብሰባውን ጀምረው እስኪ-ጨርሱ ድረስ በመጪው ምርጫ ላይ ድርጅታችን እንዲያሽንፍ ከተፈለገ ለተቃዋሚዎች ቦታ መስጠት
የለብንም፤ ካሁን ጀምሮ ማንኛውም ሰራተኛ ይህንን ለማስፈፀም ግዜውን ቢያጠፋ እንኳን ለምን ሌላውን ስራ አልሰራህም ብሎ የሚጠይቀው
አካል የለም በማለት ለሰራተኛው ፍዳውን እያሳዩት እንደሆነ መረጃው ጨምሮ ገልጿል።