Saturday, October 4, 2014

በሁሉም ግንባሮች የሚገኙ የኢህአደግ ወታደሮች ክፍላቸውን በመተው እየጠፉ በመሆናቸው በድርጊቱ ስጋት ላይ የወደቁ የበላይ አመራሮች ስብሰባ ውስጥ መጠመዳችውን ተገለጸ።



    በመቐሌ ከተማ ከሁሉም የሰራዊቱ ክፍሎች የተገኙበት ይሀው ስብሰባ በጀነራል ገብራት አየለ የተመራ መሆኑን የገለጸው መረጃው የስብሰባው አጀንዳም ድግሞ ለምን ድነው ሰራዊት በብዛት እየጠፋ ያለው የሚል እንደነበረና  በአመራሮቹ የተሰጠ መልስ ደግሞ መንግስት ለሰራዊቱ የገባላቸውን ቃል ሊተገብር ስላልቻለና ለኛ ደግሞ ውሸታሞች ስለሚቆጥሩን ነው ሲሉ መግለጻቸው ታወቀ።
   እነዚህ አዛዦች ጨምረውም ቀደም ሲል በመንግስት ለሁሉም ወታደሮች የተገባላቸው ቃል መኖሪያ ቤት እንደሚሰራላቸው፤ ማህበራዊ ኑሯቸው እንዲስተካከል የተለያዩ ጥቕማጥቅሞችም እንደሚሰጣቸው የሚሉና ሌሎችም እንደሆኑ ከገለጹ በኃላ ይሁን እንጂ ጀነራሉ በፊናው እኛ ደሞዝ ጨምረናል ችግሩ የሃላፊዎች ክትትል ማነስ ነው ሲል እንደነቀፋቸው ተገለጸ።
   መረጃው በመጨረሻ ስብሰባው ወደ ታች ወርዶ ሁሉም የሰራዊቱ አባላት እንዲወያዩበት በማለት ጀነራሉ መምርያ ካወረደ በኃላ ተሳታፊዎች በበኩላቸው   የስብሰባው አላማ ለስርአቱ ጸር ይንቀሳቀሳሉ ብለው የጠረጠርዋቸውን ሃላፊዎች ለማሰር ያለመ ነው ሲሉ እርሰበርሳቸው እየተነጋገሩበት እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።