Friday, December 19, 2014

በሽሬ ከተማ “ሃየሎም ሽሬ ባንክ ቁጥር 2” ተብሎ በሚጠራው ባንክ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተገለፀ።



   በመረጃው መሰረት በሽሬ ከተማ የሚገኝ ሃየሎም ሽሬ ባንክ ቁጥር 2 በተባለው ባንክ የAGM መለያ ያለው የባንክ ካርድ ቁጥር እየተሞላ ገንዘብ ከሚወጣበት ሳጥን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ክብሪት ይዘው በመግባት በካርድ የሚሰራውን የገንዘብ ሳጥን ለማቃጠል እሳት እንዳስገቡበት ከገለፀ በኋላ ለማቀጣጠያ የተጠቀሙበት ነዳጅ ብርቱ ሽታ ስለፈጠረ የባንኩ ዘበኞች ደርሰው የተቀጣጠለውን እሳት እንዳጠፉት ለማወቅ ተችሏል።
 እኒህ እሳት ያስነሱ ሰዎች ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ከድሃው ህዝብ ህጋዊ ባልሆነ የወለድ ብድር ውሰዱ እያለ መመዝበሪያ ከሚጠቀምባቸው ድርጂቶች አንዱ በመሆኑ በዚህ የተናደዱ ገንዘብና ሰነድ የያዘውን ሳጥን ለማቃጠል የፈፀሙት ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።