ከከተማዋ የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው የማይ ካድራ ከተማ ህዝብ ለረዥም
ግዜ መብራት ሃይል ይፈታልን እያለ ሲጠይቅ ቆይቶ ባለፈው አመት መብራት ቢገባለትም ብዙ ሳይቆይ የከተማዋ ትራንስፎርመር በመቃጠሉ
ምክንያት ነዋሪውን ህዝብ በተለይ ደግሞ የንግድ ባለቤቶች በጣም ተቸግረው እንዳሉ በተደረገላቸው ስብሰባ ላይ መናገራቸው ተገለጸ።
በስብሰባው ላይ ሃሳባቸውን ከገለፁት ዜጎች ለመጥቀስ አቶ ፍስሃ ገብረመስቀል፤
አቶ ግርማይ አስመላሽ፤ ወ/ሮ ወዘፍ ታፈርና ሌሎችም ሲሆኑ እንደ እነዚህ ወገኖች አገላለፅ መንግስት የመሰረተ ልማት ተጠቃሚዎች
አድርጎ ያቀረበውን ሪፖርት ትክክል አይደለም፣ በከተማው መብራት ከጠፋ ከአንድ አመት በላይ ማስቆጠሩና አሁንም የተሌፎን አገልግሎት ተጠቃሚ አልሆንም ሲሉ ችግራቸውን አምርረው ቢያቀርቡም
የመድረኩ አመራሮች ግን ከመስማት ውጭ ሌላ ምላሽ እንዳልሰጡዋቸው ሊታወቅ ተችሏል።