Wednesday, December 10, 2014

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በምትገኘው ገለባት በተባለች የሱዳን መሬት ላይ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግና በሱዳን ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሁለቱም ወገኖች 7 ፖሊሶች መሞታቸው ተገለፀ።



   ባገኘነው መረጃ መሰረት ህዳር 23/ 2007 ዓ/ም በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ላይ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎችን እንቆጣጠራለን በሚል በስርቆት ስራ ላይ የተሰማሩ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተላላኪ ፖሊሶች የኮንትሮባንድ ነጋዴ አግኝተናል ብለው ጥይት በተኮሱበት ጊዜ ከሱዳን ፖሊሶች ጋር ስለተጋጩ ከኢህ.አ.ዴግ ፖሊሶች መካከል አሊ መሃመድ እና ምስግና አለባቸው የተባሉት የሚገኙባቸው 4 አባሎች የሞቱ ሲሆን ሁለት መቁስላቸውና ከሱዳን ፖሊሶች ደግሞ 3 የፖሊስ አባላት እንደሞቱ ሊታወቅ ተችሏል።
   በተጨማሪም ግጭቱ ከተከሰተ በኃላ በአካባቢው ሃይለኛ ውጥረት በመንገሱ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ እለታዊ ኑሮውን ለመምራት ተቸግሮ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።