ይህ በኣማራ ክልል ባህርዳር
ከተማ ከህዳር 16 እስከ 20/ 2006 ዓ.ም በተካሄደው ውይይት። ከ168 ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች የተገኙ ሲሆን። ከያንዳንዱ
ወረዳ ግንባር ቀደም የሆኑ አባወራዎች፤ ከአንደኛ እስከ ሰወስተኛ ለወጡ የጤና ጣብያ ኬላዎች፤ ሰዎስት የወረዳ ካብኔዎችና አንዳንድ
ከጤና ኤክስተንሽን የተወከሉ። በጠቅላላ ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች በጣና ሃይቅ የስብሰባ አዳራሽ የተገኙ ሲሆኑ። ዋናው የመወያያው
አጀንዳም የክልሉ የጤና ፅህፈት ቤት ባለፈው 20 አመታት የፈፀማቸው ስራዎች ማእከል ያደረገ የስራ ክንዋኔ ማቅረብና። ከ10 በላይ
የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሌሎች ተሰታፊ አካላት። ጥናታዊ ፅህፎች ለማቅረብና ለመቀበል ያተኮረ ወይይት እንዲካሄድ ታስቦ
የተደረገ ቢሆንም። በስራ አፈፃፀሙና አቅራረቡ የተከተሉት አካሄድ ግን ቅንነት የጎደለው ስለነበረ። መድረኩ ገና ለገና ወደ ግርግርና
ተቃውሞ እንዳመራ። ከተሳታፊዎች የደረሰን መረጃ ኣስታውቀዋል፣
በክልሉ
ጤና ቢሮ ፅ/ቤት ስለ አማራ ክልል የቀረበው ያለፈው 20 አመታት የሚዳስስ የስራ አፈፃፀም። መሰረት በሌለው አሃዝ ተደርድሮ ህዝቡ
በጤና አጠባበቅ በኩል በቂ ድጋፍ እንዳገኘና። ህዝቡን የሚያገለግሉ ከበቂ በላይ ባለሞያዎችና ድርጅቶች። በሁሉም አካባቢዎች እንዳሉ
አስመስለው ያቀረቡት ሪፖርት። በተለይም ተሰብሳቢው ወደ ተቃውሞ ሊያመራው
የቻለበት ዋና ምክንያት። ፅ/ቤቱ በክልሉ ውስጥ ያለው የመከላከልና ሂወትን የማዳን ሁኔታ ከ94 % በላይ እንደተመዘገበ ተደርጎ
በቀረበበት ግዜ። ሁሉም ተሳታፊ ተቃውሞ እንዳሰማ ለማወቅ ተችለዋል፣
ተሰብሳቢዎቹ በተቃውማቸው
ከገለፁት መሰረታዊ ነጥቦች። በአማራ ክልል የጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚሰሩ ሞያቶኞች። በጥቅምና በወገንነት የሚሰሩ ከመሆናቸው
ባሻገር። ጥራቱና ደረጃው የጠበቀ መድሃኒት ያለማቅረብ፤ ሊታከም ለሄደ በሽተኛ ከሃኪም ስነ ምግባር ውጭ የሆነ አያያዝ ማድረግ፤
በጉቦና በጥቅም በመደለል በሰው ህይወት መጫወት፤ እናቶች ተገቢው ክትትል ስለ ማይደረግላቸው ህይወት ለመስጠት ህይወታቸውን እያጡ
መሆናቸው፤ ህፃናቶች በተላላፊ በሽታዎች እየሞቱ ባሉበትና የሞት ቁጥር
ባልቀነሰ ግዜ። በየትኛው ሳይንሳዊ መለክያ ነው 94 ፐርሰንት እድገት ተመዝግበዋል የምትሉት በማለት። የክልሉ ፕረዚደንት አቶ አያሌው
ጎበዜ ላቀረቡት የፓነል ውይይትና ጥናታዊ ፅሁፍ በመቃወም። ሳይስማሙ ስብሰባው እንደተበተነ መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል፣