Wednesday, December 10, 2014

ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን ከትህዴን ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ህዳር 18 2007 ዓ/ም በርካታ ወገኖችን እንዳሰረ ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን ንፁሃን ሰዎችን የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው ከተለያዩ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት እያሰረ መቆየቱን የገለፀው መረጃው በቅርቡ ደግሞ በትግራይ ክልል በሰሜናዊ፤ በማዕከላዊና በምዕራብ ዞኖች ከትህዴን ጋር በመገናኘት ሙሉ ድጋፍ ስታደርጉ ቆይታችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት ባልዋሉበት ወንጀል አስረው በከባድ ምርመራ  እያሰቃዩአቸው እንደሚገኙ ታውቋል።
  በእስር ቤት ታስረው ከሚሰቃዩ ወገኖች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ግደይ ካህሳይ ነዋሪነቱ ሽሬ እንዳስላሴ የሆነ ይርጋ ሃይለ ነዋሪነቱ አክሱም ከተማ የሆኑና ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ በርካታ ዜጎች ሲሆኑ በተለያዩ የህዝብ ስብሰባዎች የስርዓቱን ብልሹ አሰራር ይቃወሙ የነበሩ በመሆናቸው በስርዓቱ ካድሬዎች አይን ገብተው የቆዩ ሲሆን ከታሰሩ በኋላ ደግሞ ከትህዲን ጋር ስንተባበር ቆይተናል ብላችሁ በህዝብ ስብሰባ ላይ ራሳችሁን ንቀፉ ቢሏቸውም  የትህዴን አባል ስላልነበርን አንናገርም ስላሉ ብቻ በከፋ ስቃይ እንደሚገኙ ታውቋል።
  በመጨረሻም በትግራይ ክልል ለስርዓቱ ያሰጉኛል ያላቸውን የአረና አባላት ከትህዴን ጋር ትገናኛላችሁ በማለት አፍኖ የወሰዳቸውን ዜጎች ቤተሰቦቻቸው ጠይቀው እስካሁን የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉ መረጃው አስረድቷል።