በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማና
አካባቢዋ የሚኖረውን ድሃ ህብረተሰብ በየአመቱ በግዴታ ውጣ እየተባለ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በመስራቱ የተነሳ ማህበራዊ
ህይወቱን ለመምራት እጅግ ተቸግሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው፤ በዚህ የተማረረው ህዝብ ቸግሮናል ብሎ በሚቀርበት ሰዓት የአካባቢው
አስተዳዳሪዎች በቅጣት መልክ ከ70 ብር በላይ እያስከፈሉት እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል።
ከድሃው ማህበረሰብ በቅጣት መልክ የተሰበሰበ ገንዘብ በልማታዊ ስራዎች
ሳይውል በሙስና የተጨለቁ በአካባቢው በሚገኙ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች እየተበላ መሆኑን ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል።