እነዚህ ለረጅም ዓመታት በትግልና በውትድርና ስራ ላይ ተሰማርተው ከቆዩ
በኋላ በጡረታ የተሰናበቱ ዜጎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ህይወታቸውን ለመምራት በጽሕፈት ቤቶች እንዲቀጠሩና የስራ እድል እንዲፈቀድላቸው
ያቀረቡት ጥያቄ በስርአቱ ካድሬዎች ተቀባይነት እንዳለገኘ ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።
ታጋዮቹና ወታደሮቹ በተደጋጋሚ በደብዳቤና በአካል እስከ ክልል ቢሮ ድረስ በመሄድ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ላቀረቡት ጥያቄ ውጤት እንዳላገኙበት
የገለፀው መረጃው የዚህ ምክንያትም በመንግስት መስሪያ-ቤት ውስጥ ተቀጥረው እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው የሚታየውን የስራ ድክመት ወደ
ህዝቡ በማቅረብ የማነሳሳት ተግባር ሊፈፅሙ ይችላሉ በሚል ስጋት እንደሆነ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።