በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች በምግብ
እጥረት፤ የሚጠጣ ውሃ፤ የመብራትና ሌሎችም ማህበራዊ ችግሮች ስላጋጠማቸው ትምህርታቸውን ሊከታተሉ አለመቻላቸው የገለጸው መረጃው፤
አጋጥሞ ላለው የማህበራዊ ኑሮ ችግር እንዲፈታላቸው በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡት ጥያቄ ሰሚ ጀሮ ስላላገኘ ጠንካራ
የተቃውሞ ሰልፍ ማስነሳታቸውና ይህንን አድማ ለመበተን የፌደራል ፖሊስ
ወደ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ በመግባት ሓይል የተሞላበት እርምጃ በተማሪዎች ላይ እንደወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
በተለይ አጋጥሞ
የቆየውን የውሃ እጥረት እንዲፈታ ተብሎ ለውሃ ጉድጓድ መቆፈርያ እንዲውል የተመደበውን በጀት አስተዳዳሪዎች ለግል ጥቅማቸው ስላዋሉት
ተቆፍሯል የተባሉት የውሃ ጉድጓዶችም በተገቢው መንገድ ስላልተሰሩ ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ማስተማር ከጀመረ ጀምሮ የተመደበልንን በጀት አልተጠቀምንበትም፤
በዩኒቨርስቲው አመራሮች እየተበላ ነው። በከባድ የማህበራዊ ችግር እየተሰቃየን ነው በማለት ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ እያነሱ መምጣታቸውን
ባለፈው የዜና እወጃችን ማሳወቃችን ይታወሳል።