Wednesday, December 10, 2014

የአክሱም ከተማ አስተዳዳሪዎች ለከተማው ልማት ተብሎ የተመደበውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸው ተገለጸ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአክሱም ከተማ ከንቲባ አቶ አበራ ሃይለማርያም ከከተማው ፀጥታ ሃላፊ ጋር በመስማማት ለህዝቡ የልማት አገልግሎት እንዲውል ተብሎ በከተማው ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀው በጀት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን በላይ ብርና ተሌብዥን ላፕቶፕና የመሳሰሉትን ንብረቶች ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    መረጃው ጨምሮም የህወሃት ኢህአዴግ  ገዢዎች የህዝብንና የሃገርን ንብረት እያጠፋፉ መሆናቸውን የተረዳው የከተማው ነዋሪ ህዝብ በህግ ፊት ቀርበው ይጠየቁ ብሎ በተናገረው መሰረት ለማስመሰል ሲባል ብቻ መታሰራቸውን የገለፀው መረጃው፣ ይህንን ለማድረግ ያስገደደውም የአባይ ወልዱ እጅ ስላለበት  እስካሁን እየተከላከለላቸው መቆየቱንና በዚህም ድርጊት ነዋሪው ህዝብ በአባይ ወልዱ ብልሹ አሰራር ላይ ምሬቱን እያሰማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
    የአክሱም ከተማ ጥንታውያን ከተሞች ከሚባሉና የስልጣኔ መሰረት ከሆኑት የሃገራችን ከተማዎች በቀዳሚነት የምትቀመጥ ብትሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን ከቱሪዝም ከምታገኘው ከፍተኛ ገቢ ጋር ሲነፃፀር በእድገት ወደ ኋላ ከቀሩ የሃገረችን ከተሞች አንዷ ሆና እንደምትገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።